የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት፤
ኢትዮጵያ የተባለችው፤
አንደኛ እናትህ ናት፣
ሁለተኛ ክብርህ ናት፣
ሦስተኛ ሚስትህ ናት፣
አራተኛ ልጅህ ናት፣
አምስተኛ መቃብርህ ናት።
እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣
የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባድነት እንደዚህ መሆኑን እወቅ!
አፄ ዮሐንስ ፬ኛ